
የልደት ምኞት አጭር፣ አስቂኝ፣ ግላዊ ወይም እነዚህን ያጣመረ ሊሆን ይችላል። ለጓደኛዎ የልደት ምኞት እንዴት እንደሚገልጹ እያሰቡ ከሆነ፣ በተለምዶ እንዴት እንደምትነጋገሩ ያስቡና የሚስማማ መልዕክት ይምረጡ። በአካል አብራችሁ ማክበር ካልቻላችሁ፣ ምኞትዎን በimo ይላኩ፣ የድምፅ መልዕክት ይላኩ ወይም የቪዲዮ ጥሪ ያድርጉ።
ለጓደኞች አጭር የልደት ምኞቶች
መልዕክትዎን ቀላልና ወዳጃዊ ማድረግ ሲፈልጉ እነዚህ አጭር የልደት ምኞቶች ተስማሚ ናቸው።
- መልካም ልደት! ደስ የሚል ቀን እንዲኖርህ እመኛለሁ።
- መልካም ልደትና አስደሳች የወደፊት ዓመት እመኝልሃለሁ።
- መልካም ልደት! ዛሬ ብዙ መልካም ጊዜያትን እንዲያመጣልህ እመኛለሁ።
- ደስታ፣ ጤናና ፈገግ የምትልባቸው ብዙ ምክንያቶች እመኝልሃለሁ።
- በጣም ከምወዳቸው ሰዎች ለአንዱ መልካም ልደት!
- በዚህ ዓመት የተመኘኸውን ሁሉ እንድታገኝ እመኛለሁ። መልካም ልደት!
- ድንቅ የልደት ቀን ይሁንልህ። መልካም ቀን ይገባሃል።
- መልካም ልደት! ቀንህን በደስታ አሳልፍ፤ ለእኔም አንድ ተጨማሪ ቁራጭ ኬክ ብላ።
- በጥሩ ምግብ፣ በጥሩ ሰዎችና በሚያምሩ ትዝታዎች የተሞላ ልደት እመኝልሃለሁ።
- መልካም ልደት! ይህ ዓመት መልካም እንዲሆንልህ እመኛለሁ።
- ዛሬ ብዙ የልደት ምኞቶችን እልክልሃለሁ።
- የልደት ቀንህ ልክ እንደምትፈልገው እንዲሆን እመኛለሁ።
- መልካም ልደት! ተደሰት፣ ቀንህንም በሚገባ ተጠቀምበት።
- መልካም ልደትና ብዙ መልካም ቀናት እመኝልሃለሁ።
- መልካም ልደት! በቅርቡ አብረን ለማክበር እንድንችል እመኛለሁ።
ለቅርብ ጓደኛ ልባዊ የልደት ምኞቶች
ለቅርብ ጓደኛዎ “መልካም ልደት” ብቻ ከማለት ይልቅ፣ የሚያደንቁትን ነገር፣ የምትጋሩትን ትዝታ ወይም አብራችሁ ያሳለፋችሁትን ነገር ይጥቀሱ።
- ሁልጊዜ ልተማመንበት ለምችለው ሰው መልካም ልደት። ጓደኛሞች በመሆናችን በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ይህ ዓመትም ብዙ መልካም ነገሮችን እንዲያመጣልህ እመኛለሁ።
- ብዙ መልካም ቀናትን፣ እንግዳ ቀናትንና በመካከላቸው ያሉትን ሁሉ አብረን አሳልፈናል። መልካም ልደት! እንደዚህ ያሉ ብዙ ቀናት ወደፊትም ይኑሩን።
- መልካም ልደት! የማወራው፣ አብሬው የምስቀው ወይም ዝም ብዬ ጊዜ የማሳልፍበት ሰው ሲያስፈልገኝ ከጎኔ ስለነበርክ አመሰግናለሁ።
- ጓደኝነትህ ለእኔ ምን ያህል ትርጉም እንዳለው እንደምታውቅ ተስፋ አደርጋለሁ። እጅግ ደስ የሚል ልደትና ለምትወዳቸው ነገሮች ተጨማሪ ጊዜ የሚሰጥህ ዓመት ይሁንልህ።
- የተለያዩ ገጽታዎቼን አይቶ በሁሉም ጊዜ ከጎኔ ለቆየው ጓደኛ መልካም ልደት።
- ስለ ከባድ ጉዳዮችም ሆነ ምንም ትርጉም ስለሌላቸው ነገሮች ማውራት የምችልበት ጓደኛ በማግኘቴ ዕድለኛ ነኝ። መልካም ልደት!
- መልካም ልደት። ይህ ዓመት አስጨናቂ ቀናትን እንዲቀንስልህና ደስ የሚያሰኙህን ነገሮች በብዛት እንዲያመጣልህ እመኛለሁ።
- አንዳንድ ጓደኝነቶች ጊዜ ባለፈ ቁጥር ይበልጥ ምቹ ይሆናሉ። የእኛም ከእነዚያ አንዱ በመሆኑ ደስ ብሎኛል። መልካም ልደት!
- ዛሬን ምቾት ከሚሰማህ፣ ዋጋ ከሚሰጡህና ሙሉ በሙሉ ራስህን መሆን ከምትችልባቸው ሰዎች ጋር እንድታሳልፍ እመኛለሁ።
- መልካም ልደት። ረጅም ንግግር የለኝም፤ በሕይወቴ ውስጥ በመኖርህ በጣም ደስተኛ መሆኔን ብቻ ላስታውስህ።
ለጓደኞች አስቂኝ የልደት ምኞቶች
አስቂኝ የልደት ምኞቶች ዕድሜ ስለመጨመር፣ ስለ ኬክ፣ ስለ ያልተሳኩ ውሳኔዎች ወይም ሁልጊዜ አብራችሁ ስለምትቀልዱባቸው ልማዶች ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚያ ጓደኛ ጋር በተለምዶ የምትቀልዱበትን ዓይነት ይምረጡ።
- መልካም ልደት! አላረጀህም። “ያኔ ትዝ ይለኛል…” ብለው የሚጀምሩ ታሪኮችህ ብቻ በዝተዋል።
- ሌላ የልደት ቀን፣ ከእራት በፊት ኬክ ለመብላትም ሌላ በቂ ምክንያት።
- መልካም ልደት! ውድ ስጦታ ልገዛልህ አስቤ ነበር፣ ግን ይህ መልዕክት ለኪሴ የተሻለ ምርጫ ሆነ።
- የራስህን ውሳኔዎች እየተቋቋምክ ሌላ ዓመት ስላለፍክ እንኳን ደስ አለህ!
- መልካም ልደት! ዛሬ ኬክህ ከኃላፊነቶችህ ዝርዝር የበለጠ ትልቅ ይሁን።
- አንድ ዓመት ጨመርክ፤ ቀልዶችህ ግን አሁንም ምንም አልተለወጡም።
- መልካም ልደት! ዛሬ ስለ አሳፋሪ ታሪኮችህ ምንም እንዳላስታውስህ ቃል እገባለሁ። ነገ ግን ሌላ ቀን ነው።
- ሌላ ዓመት በሰላም አለፍክ። ይህ ቢያንስ ሁለት ቁራጭ ኬክ የሚያስገኝልህ ይመስለኛል።
- ስለ እኔ ብዙ ነገር ስለምታውቅ ከእንግዲህ ጓደኛዬ መሆንህን ማቆም አትችልም። መልካም ልደት።
- ስለ ዕድሜህ ቀልድ እናገር ነበር፤ ግን በሚቀጥለው ልደትህም መጋበዝ እፈልጋለሁ።
ለምርጥ ጓደኛዎ የልደት ምኞቶች
ለቅርብ ጓደኛዎ የሚልኩት መልዕክት አስቂኝ፣ ግላዊ ወይም በቀላሉ ከተለመደው የንግግር ዘይቤዎ ጋር የሚስማማ ሊሆን ይችላል።
- ለምርጥ ጓደኛዬና አብዛኛዎቹ የዘፈቀደ መልዕክቶቼ ለሚደርሱት ሰው መልካም ልደት።
- ያለአንተ ሕይወት በጣም ጸጥ ትል ነበር፤ ግን በፍጹም የተሻለች አትሆንም። መልካም ልደት!
- መልካም ዜና፣ መጥፎ ዜና ወይም ምንም ዜና ሳይኖረኝ እንኳ ልደውልለት ለምችለው ጓደኛ መልካም ልደት።
- ለዓመታት እርስ በርሳችንን ለማሳፈር የሚበቁ ትዝታዎች አሉን። መልካም ልደት! ጥቂት ተጨማሪ እንፍጠር።
- ተመሳሳይ ታሪኮቼን ከአንድ ጊዜ በላይ ሰምቶም አሁንም እንደሚያዳምጠኝ ለሚያስመስለው ሰው መልካም ልደት።
- ይህ ዓመት ከምትፈልገው ነገር የበለጠ፣ ጉልበትህን ከሚያሟጥጠው ደግሞ ያነሰ እንዲሰጥህ እመኛለሁ። መልካም ልደት።
- አብሬው ዕቅድ ማውጣት፣ ዕቅዱን መሰረዝና ከዚያም ስለ አዲስ ዕቅድ ማውራት ለምወደው ሰው መልካም ልደት።
- ሕይወት ምንም ያህል በሥራ ቢያጨናንቀንም፣ ካቆምንበት መቀጠል መቻላችን ደስ ይለኛል። መልካም ልደት!
- መልካም ልደት። ከአንተ ጋር ስሆን ራሴን መሆን ስለምችል አመሰግናለሁ።
- አብረን የምናከብረው ሌላ የልደት ቀን። ምንም እንኳ ከእንግዲህ ቁጥሩን በዝርዝር ባንቆጥረው የተሻለ ቢሆንም፣ እኔ ግን እየተከታተልኩ ነው።
በሩቅ ለሚኖር ጓደኛ የልደት ምኞቶች
ጓደኛዎ ርቆ የሚኖር ከሆነ፣ ሙሉ መልዕክቱን ስለ ርቀት ሳያደርጉት አብረው መሆን እንደሚፈልጉ መጥቀስ ይችላሉ።
- ከሩቅ መልካም ልደት! ዛሬ በአካል ከአንተ ጋር ማክበር ብችል ደስ ይለኝ ነበር።
- በተለያዩ ቦታዎች ልንሆን እንችላለን፤ ዛሬ ግን አስብሃለሁ። መልካም ልደት!
- መልካም ልደት! በአንድ ከተማ የምንገናኝበትን ቀጣይ ጊዜ ጠብቀን በሚገባ እናከብረዋለን።
- መልዕክት ከመላክ ይልቅ ኬክ ማምጣት ብችል ደስ ይለኝ ነበር። ድንቅ የልደት ቀን ይሁንልህ!
- ከሩቅ መልካም ልደት። ቀንህ በጥሩ ሰዎች፣ በጥሩ ምግብ እንዲሞላና ምንም የሥራ መልዕክት እንዳይደርስህ እመኛለሁ።
- በተለያየ ከተማ ብንሆንም፣ ልደትህን ግን አልረሳሁም። በጣም ጥሩ ቀን ይሁንልህ።
- መልካም ልደት! በድግሱ ላይ ላልገኝ እችላለሁ፤ ፎቶዎችን ግን እጠብቃለሁ።
- ዛሬ ከአንተ ጋር መሆን ብችል ደስ ይለኝ ነበር። እስከዚያው ይህን መልዕክት ከሩቅ እንደተላከ የልደት እቅፍ ቁጠረው።
በimo የልደት ቪዲዮ ጥሪን የበለጠ አስደሳች ያድርጉ
ጓደኛዎ ስጦታ ሲከፍት፣ የልደት ኬኩን ሲቆርጥ ወይም ከድግሱ ትንሽ ዕረፍት ሲወስድ በimo ሊደውሉለት ይችላሉ። በአካል አብራችሁ ማክበር በማትችሉበት ጊዜ፣ አጭር ጥሪ እንኳ በቂ ሊሆን ይችላል።
በቪዲዮ ጥሪው ወቅት Light አዶውን ይንኩና የልደት ገጽታ ያለውን ፍሬም ይምረጡ። ፍሬሙ በጥሪው ላይ የልደት ድባብ ይጨምራል፣ ፊትዎም የበለጠ ብሩህ እንዲታይ ይረዳል።
መልዕክቱን አጭር ማድረግ ቢፈልጉም የበለጠ የበዓል ድባብ እንዲኖረው ከፈለጉ፣ ከጥሪው በፊት ወይም በኋላ በውይይቱ ውስጥ “መልካም ልደት” የሚል ተለጣፊ ምስል መላክም ይችላሉ።

የልደት ምኞትዎን ግላዊ ያድርጉ
ከላይ ካሉት የልደት ምኞቶች አንዱን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የበለጠ ግላዊ እንዲሆን አንድ ወይም ሁለት ዝርዝሮችን ይለውጡ።
በእውነት የተከሰተን ነገር ይጥቀሱ
ሁለታችሁም የምትጋሩትን ትዝታ ይጥቀሱ።
“መልካም ልደት! መልካም ዓመት እንዲሆንልህ እመኛለሁ” ብለው ከመጻፍ ይልቅ፣
እንዲህ ሊጽፉ ይችላሉ፦ “መልካም ልደት! ባለፈው ዓመት በዚያ ጉዞ ላይ ለሁለት ሰዓት መንገድ መሳታችንን አሁንም ማመን አልችልም። በቅርቡ እንደገና የሆነ ቦታ መጓዝ አለብን።”
በተለምዶ የሚናገሩበትን ዘይቤ ይጠቀሙ
በተለምዶ ጓደኛዎን በቅጽል ስም የሚጠሩት ከሆነ፣ ያንኑ ይጠቀሙ። ውይይቶቻችሁ በአብዛኛው ዘና ያሉ ከሆኑ፣ በጣም መደበኛ የልደት አንቀጽ እንግዳ ሊመስል ይችላል። ለኢሞጂም ተመሳሳይ ነው። በተለምዶ ኢሞጂ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ጥቂቶቹን ይጨምሩ። ካልሆነ ግን፣ ልደት ስለሆነ ብቻ መልዕክቱን በኬክና በፊኛ ኢሞጂዎች መሙላት አያስፈልግም።
የሚመኙላቸውን ነገር በግልጽ ይግለጹ
“መልካሙን ሁሉ እመኝልሃለሁ” የሚለው ጥሩ ነው፤ ግልጽና የተወሰነ ምኞት ግን የበለጠ ግላዊ ስሜት ሊሰጥ ይችላል።
- አዲስ ሥራ እየፈለገ ከሆነ፦ “መልካም ልደት! በእውነት የምትወደውን ሥራ የምታገኝበት ዓመት እንዲሆንልህ እመኛለሁ።”
- ጉዞ እያቀደ ከሆነ፦ “መልካም ልደት! ስታወራለት የነበረውን ጉዞ በመጨረሻ ማድረግ እንድትችል እመኛለሁ።”
- ላለፉት ጥቂት ወራት ውጥረት አሳልፎ ከሆነ፦ “መልካም ልደት። ይህ ዓመት ዘና ለማለት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥህ እመኛለሁ።”
መልዕክቱን ከሚያስፈልገው በላይ አያራዝሙ
የልደት መልዕክት ረጅም መሆን አያስፈልገውም። ጥቂት ግላዊ ሐረጎች በቂ ናቸው።
ቀሪውን ለimo የቪዲዮ ጥሪ ያስቀምጡት። መጀመሪያ አጭር መልዕክት ይላኩ፤ ከዚያም ጓደኛዎ ነፃ ሲሆን ይደውሉ። መልካም ልደት እያሉ ምኞትዎን ሲገልጹ ወይም ጓደኛዎ ስጦታ ሲከፍት ሲመለከቱ፣ በLight አዶ በኩል የልደት ገጽታ ያለውን ፍሬም ይምረጡ።